Welcome to Lideta Subcity Youth and Sport Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ እና ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ተፈጥሮ ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

«በጎነት መገለጫችን፤ ደማችን ለወገናችን» በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሄደ

ሀምሌ 16/11/2018 ዓ.ም, 2018
«በጎነት መገለጫችን፤ ደማችን ለወገናችን» በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሄደ** በልደታ ክፍለ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት **«በጎነት መገለጫችን፤ ደማችን ለወገናችን»** በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የደም ልገሳ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል። በዚሁ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ላይ የክፍለ ከተማው የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዘመኑ ደሳለኝ እና የወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ግዛው አለሙ ተገኝተው ደማቸውን በመለገስ አርአያነታቸውን አሳይተዋል። አመራሮቹ ባስተላለፉት መልእክት፤ ደም መለገስ የሰዎችን ሕይወት ከመታደግ ባሻገር የወገን አለኝታነት እና የደግነት መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። ወጣቱም በተለያዩ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዎች ላይ እያደረገ ያለውን ንቁ ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። በመርሃ ግብሩ በርካታ የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ተሳታፊ በመሆን በበጎ ፈቃደኝነት ደም በመለገስ ላይ ይገኛሉ።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች