Welcome to Lideta Subcity Youth and Sport Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ እና ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ተፈጥሮ ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

በልደታ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኙ የታዳጊ ወጣቶችን የስፖርት ተሰጥኦ ለማውጣትና ስነ-ምግባርን ለማጎልበት ያለመው “6ኛው ከ13 እና ከ15 ዓመት በታች የታዳጊዎች የእግር ኳስ ውድድር” ተጀምራል።

ሰኔ 25/10/18, 2018
በልደታ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኙ የታዳጊ ወጣቶችን የስፖርት ተሰጥኦ ለማውጣትና ስነ-ምግባርን ለማጎልበት ያለመው “6ኛው ከ13 እና ከ15 ዓመት በታች የታዳጊዎች የእግር ኳስ ውድድር” ተጀምራል። የክፍለ ከተማው የወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግዛው አለሙ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት “ዛሬ የምንከፍተው ውድድር ከዋንጫ ውድድር በላይ ትልቅ ትርጉም አለው” ካሉ በኋላ፣ ይህ መድረክ የወደፊት የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ተስፋዎችን የምናይበት፣ ተሰጥኦ የምናበረታታበት፣ ወጣቶች የትብብር፣ የሥነ-ምግባር፣ የመከባበር እና የፍቅር እሴቶችን በተግባር የሚማሩበት አስፈላጊ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ዮናስ ሰለሞን የስፖርት ማህበራት ማደራጃትና ውድድር ቡድን በበኩላቸው የዚህ ውድድር ዋና ዓላማ ታዳጊዎችን ከአደገኛ ሱሶችና ከአሉታዊ ተግባራት በመጠበቅ ወደ ስፖርት እንዲቀርቡ፣ ተሰጥኦአቸውን እንዲያዳብሩ እና ለሀገር የሚጠቅሙ ተጫዋቾች እንዲሆኑ መሠረት መጣል መሆኑን አስገንዝበዋል። ይህንን ታላቅ የክረምት ወቅት የስፖርት መድረክ እውን ለማድረግ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ለሁሉም ድጋፍ ሰጪዎች የጽሕፈት ቤት ኃላፊው የላቀ ምስጋና አቅርበዋል። በውድድሩም ላይ አመራሮች አሰልጣኞች፣ ዳኞች፣ ወላጆች እንዲሁም በርካታ ቁጥር ያላቸው ታዳጊ ተጫዋቾችና የስፖርት አፍቃሪያን ተገኝተዋል። በመጨረሻም 6ኛው የልደታ ክፍለ ከተማ የታዳጊዎች እግር ኳስ ውድድር በሰላም፣ በፍትሃዊነት፣ በወዳጅነትና በታላቅ ስኬት እንዲጠናቀቅ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች