Welcome to Lideta Subcity Youth and Sport Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ እና ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆነ ስፖርተኛ ተፈጥሮ ለማየት ይተጋል!!

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

በልደታ ክፍለ ከተማ በርካታ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች የሚካሄዱባት የፌዴራሉ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫና በርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ተቋማት የሚ ገኙባት በመሆኑ የወጣቶችን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ማሳደግና ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ፣ ጤናማ ዜጋ ፣ ብቃት ያለው ስፖርተኛና ህብረተሰብን በመፍጠር የከተማዋን የሰላም ፣ የልማትና የዴሞክራሲ እድገት ማፋጠን ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው፡፡

ወጣቶች በሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ከማንኛውም ዜጋ በላይ ከፍተኛ ድርሻ ሊወጡ የሚችሉ ሀገር ገንቢና ተረካቢ፣ የነገ ተስፋዎችና በአገራችንም ሆነ በክፍለ ከተማችን በሚካሄዱ የልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሪ ተዋናይ መሆናቸው እሙን ነው፡፡ በተመሳሳይም ስፖርት ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት የሚያበረክተው አስተዋጾ ጉልህ ሲሆን በዘርፉ የስራ እድል ከማስገኘት ባሻገር ጤናማና አምራች ዜጋ በመፍጠር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ በልደታ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ፖሊሲውን መሰረት ያደረገ የወጣቶች የልማትና የእድገት ፓኬጅ ... ተጨማሪ ያንብቡ

አቶ አንተነህ በፍቃዱ , የልደታ ክ/ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡